Fana: At a Speed of Life!

ከፑሽኪን አደባባይ -ጎፋ ማዞርያ- ጎተራ ማሳለጫ እየተገነባ ያለው መንገድ 77 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሌክሳንደር ፑሽኪን አደባባይ ተነስቶ በጎፋ ማዞርያ ጎተራ ማሳለጫ እየተሰራ ያለው መንገድ በታቀደው ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡
በ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ከቻይና መንግሥት በተገኘ ብድር ነው ግንባታው እየተካሄደ ያለው፡፡
ፕሮጀክቱ በ2012 የተጀመረ ሲሆን÷ በሁለት ዓመት ከስድስት ወር ለማጠናቀቅ ታስቦ ነው እየተሰራ ያለው፡፡
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢያሱ ሰለሞን÷ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳብራሩት የመንገዱ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር እርዝመት ያለው እና የጎን ስፋቱ ከ30 እስከ 45 ሜትር የሚደርስ ነው።
በሁለት አቅጣጫ 320 ሜትር እርዝመት የሚደርስ ዋሻ ያለው መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
እስካሁንም ፕሮጀክቱ 77 በመቶ የደረሰ ሲሆን÷ በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል።
ካለው የትራፊክ መጨናነቅ የተነሳ በተወሰነ መልኩ ለትራፊክ ክፍት መደረጉን ጠቅሰው÷ ተሽከርካሪዎች እና እግረኞች የግንባታ ስራው ባለመጠናቀቁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ምክትል ዋና ዳሬክተሩ አሳስበዋል።
በቀሩት ስድስት ወራት መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለትራፊክ ክፍት ይደረጋል ተብሏል።
በሲሳይ ጌትነት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.