Fana: At a Speed of Life!

የመውሊድን በዓል በወንድም ካሊድ ፋዉንዴሽን ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ወንድም ካሊድ ከራስ በላይ ለሌሎች መኖርን በተግባር ያሳየ ቀና ልብ ያለው ወጣት ነዉ አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ።
1 ሺህ 496 ኛዉን የመውሊድ በዓልን ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሣሕለወርቅ ዘውዴ፣ ከተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ወገኖቻችን፣ ኢትዮጵያን የክፉ ቀን ቤቴ ብለዉ በከተማችን ከሚኖሩ አቅመደካማ ሶሪያዉያን ስደተኞችና ቤተሰቦች ጋር በወንድም ካሊድ የምግባረ ሰናይ ፋዉንዴሽን ቅጥር ጊቢ መአድ በማጋራት አክብረናል ብለዋል ወ/ሮ አዳነች አቤቤ።
ኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በመከላከል፣ በየጎዳናው የወደቁ አቅመ ደካምችን በማንሳት፣ የአረጋውያንና አቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ ኑሯቸውን በዘላቂነት በማሻሻል ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣት የቻለ እና ለሌሎችም በርካታ ወጣቶች አርአያ የሆኑ ተግባራትን ማከናወን የቻለ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ለዚህ መልካም እና አርአያነት ያለው ተግባር ቀጣይነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለፋዉንዴሽኑ የሚያደርግ ሲሆን ዛሬም የመዉሊድ በዓልን አስመልክተን 20 በጎችን ይዘን እንኳን አደረሳችሁ ብለናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.