የኢትዮጵያን አቅምና ዕውነታ መረዳት እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን አቅምና ዕውነታ መረዳት እንደሚገባው የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ አሳሰቡ፡፡
የአፍሪካ ልጆች ያላቸውን አቅም የዓለም ማህበረሰብ መረዳት እንደሚገባውም ዶክተር ፍጹም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ፈተናዎች አቅልለን አንመለከትም ያሉት ሚኒስትሯ፥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የአገራችንን አቅምና ዕውነታ መረዳት እንደሚገባው በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አመልክተዋል።
አንዳንድ አካላት ኢትዮጵያ ያሏትን እውነታዎች በጥቂቱም ቢሆን እንዳልተረዱ ገልጸው፥ ”እነዚህን አካላት ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዚህም የአፍሪካውያንን አቅም መረዳት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ነው የገለጹት፡፡
‘’በላያችን ላይ የተጣሉብንን ሰንሰለቶች እየበጣጠስን በመወርወር ነፃነታችንን እንደጠበቅን አስታወሳችሁ?’’ በማለትም ጠይቀዋል ሚኒስትሯ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!