Fana: At a Speed of Life!

በኖርዌይ ዓለም አቀፍ የ #በቃ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና በመቃወም ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ እየተካሄደ ነው።
በሰልፉ ላይ ከኦስሎ፣በርገን፣ስታቫንገር፣ትሮንዳይምና ሌሎች የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ በአገሪቷ የሚኖሩ የአፍሪካ አገራት ዜጎችና የኢትዮጵያ ወዳጆች እየተሳተፉ ነው።
ሰልፉ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ “ሴንትራል ስቴሽን” እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ተነስቶ ወደ አገሪቷ ፓርላማ በማቅናት የሚካሄድ ነው።
“ምዕራባውያን አገራት ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ”፣ “ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የሚሰሩትን የሀሰት ዘገባ ያቁሙ፣ “የኢትዮጵያ ችግር በኢትዮጵያውያን ይፈታል፣ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” እና #በቃ የሚሉ መልዕክቶች በሰልፉ እየተስተጋቡ ነው፡፡
በኖርዌይ መዲና ኦስሎ እየተካሄደ ያለውን ሰላማዊ ሰልፍ ያዘጋጁት በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያና የኤርትራ የሲቪክ ማህበራት ናቸው ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.