Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት የተደቀነውን ስጋትና አደጋ ለመቀልበስ ዝግጁ ነን – የወንበራ የቀድሞ ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓትና በግብረ አበሮቹ አማካይነት በአገራችን ላይ የተደቀነውን ስጋትና አደጋ ለመቀልበስ ዝግጁ መሆናቸውን የወምበራ ወረዳ የቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላትና አባት አርበኞች ገለጹ፡፡
 
በቀድሞ ሰራዊት አባላት አዘጋጅነት የአገር መከላከያ ሠራዊትን እና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎችን የሚደግፍ እንዲሁም ህወሓትና ጀሌዎቹን የሚቃወም ሰልፍ በወንበራ ወረዳ ተካሂዷል፡፡
 
በድጋፍ ሰልፉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ሃምሳ አለቃ መኩሪያው ድናዴ እኛ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ትልቁ ህልማችንና መኩሪያችን አገራችን ፤ እኛ የምንኮራባት አገራችን ኢትዮጵያ ሌላ ስም የላትም ወደፊትም አይኖራትም ብለዋል፡፡
 
ሰልፉ አሜሪካንና አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት በአገራችን ጣልቃ መግባታቸውን ለመቃወምና አሸባሪዎቹን ህወሓትና የእሱ ተላላኪ የሆኑትን ሸኔና የጉህዴን ታጣቂዎችን ብሎም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ለተሰገሰጉ አጥፊዎች ስንቅና መረጃ የሚያቃብሉትን ለመቃወም ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
 
የድጋፍ ሰልፉ አዘጋጅና ተሳታፊ የቀድሞ ሠራዊት አባላት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን አገርን ከጠላት የማዳንና ጥሪን ተከትለው በተቻላቸው አቅም ያላቸውን ወታደራዊ እውቀትና ክህሎትን ተጠቅመው ወራሪውን የህወሓት ሃይልና ተላላኪዎችን ለማጥፋት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ወጣቱ የአባቶቻቸው ለጠላት አይበገሬነት መንፈስ ተላብሰው ከሁሉም የጸጥታ ኃይል ጎን መቆም እንዳለባቸው አጽንኦት መስጠታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.