በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደግንባር የሚያመሩ ባለሙያዎች ተሸኙ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሠራዊት የህክምና ድጋፍ ለመስጠት ወደ ጦር ግንባር ለሚያመሩ የሕክምና ባለሙያዎች በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሽኝት ተደርጎላቸዋል ።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታ አየለ ከዚህ ቀደም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለሰራዊት መደረጉን ገልጸው ÷ በአሁኑ ወቅት የጤና ባለሙያዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ለመከላከያ ኃይላችን ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ በመወሰናቸው አመስግነዋል፡፡
ለህክምና ባለሙያዎችንም ሆነ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል።
የህክምና ባለሙያዎቹም፥ “የመከላከያ ሰራዊቱን ለማገልገል ዕድል በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ አገርን እንደማገልገል መልካም ነገር እንደሌለ ተናግረዋል ።
በዛሬው ዕለት ዩኒቨርሲቲው ሶስት የጤና ባለሙያዎችን ለአገር መከላከያ ሰራዊት የህክምና ድጋፍ ለመስጠት አሸኛኘት ያደረገ ሲሆን፥ በቅርቡም መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በፈቃደኝነት ጥያቄ ያቀረቡ ሁለት አባላትን መሸኘቱን አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታ አየለ ዘማች የጤና ባለሙያዎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ለአገር ጥሪ ምላሽ መስጠታቸው በታሪክ ማህደር ስማቸው በጉልህ እንደሚሰፍር ጠቅሰው፥ በድል እንደሚመለሱም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ።
በማስተዋል አሰፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!