Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገራትን የገንዘብ ኖቶች ሊያባዙ የነበሩ ሰዎችእ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዪ አገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
አንድ ካሜሮናዊ እና አንድ ኮቲዲቯራዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ ፔንሲዮን ውስጥ እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት ፔንሲዮን ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ግለሰቦቹ የኢትዮጵያና የተለያዩ አገራት የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ 107 ሺህ 330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብር ኖቶች፣ የተለያዩ አገራት ገንዘቦች፣ ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣ ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣ ፈሳሽ ኬሚካሎች፣ ከተር ወይም የወረቀት መቁረጫ፣ በርካታ ቾክ፣ ወረቀት፣ 9 ሞባይል ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁስ መያዛዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መረጃ አመላክቷል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.