Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ታክሲ አሽከርካሪዎች ለመከላከያ ሠራዊት ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከ11 ሺህ በላይ የባለ ሶስት እግር የታክሲዎችና ተባባሪ ታክሲ አሽከርካሪዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሰባሰቡትን ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ።
የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ተወካይ ወጣት ቃልኪዳን ፀሐይ ድጋፉን ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና ለሠራዊቱ ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ዛሬ አስረክቧል።
የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ቀደም ሲልም ለአገር መከላከያ ሠራዊት 746 ዩኒት/ከረጢት ደም መለገሳቸውን ወጣት ቃልኪዳን አስታውሷል።
በዛረው የድጋፍ አሰጣጥ ሥነስርዓት ላይ የታክሲ አሽከርካሪዎችና የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደም ለግሰዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች አልባሳት መሰባሰቡንም ተናግሯል፡፡
የታክሲ አሽከርካሪው ስንታየሁ አራጋው በሥነስርዓቱ ላይ ”የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ጥሪ ተከትለን ግንባር በመዝመት ሀገርን ለማዳን ዝግጁ ሆነን እየተጠባበቅን ነው” ብሏል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የከተማዋ ታክሲ አሽከርካሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት በሀገር ፍቅር ስሜት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ በበኩላቸው አሽከርካሪዎቹ ለአገርና ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ከፀጥታ አካላት ጋር እያደረጉት ያለውን አብነታዊ ሥራ አጠናክረው እንደፊቀጥሉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.