የኮሌራ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲቲዩት ከዓለም አቀፍ የክትባት ኢንስቲቲዩት፣ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ኮሌራ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮጀክትን አስጀምሯል፡፡
ፕሮጀክቱ በንፁህ ውሀ እና በንፅህና አጠባበቅ ጉድለት በሚመጣው የኮሌራ በሽታ ላይ በሻሽመኔ ከተማ እና በሻሸመኔ ወረዳ በተመረጡ ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች ክትባት በመስጠት የክትባቱን ውጤታማነትና የበሽታው አጋላጭ ምክንያቶችን ለማጥናት ለሁለት ዓመታት እንደሚሰራ ታውቋል፡፡
ስራውን ለማስጀመር ይረዳው ዘንድ በዚህ የማስጀመሪያ ስነስርዓት ከተለያዩ አደረጃጀቶች ለተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የጤና ባለሙያዎች እና የነዋሪዎች ተወካዮች በተገኙበት ውይይት መደረጉን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!