Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ለህልውና ዘመቻ ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ደጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻው እንዲውል ያሰባሰቡትን ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉን ያስከቡት ተቋማት÷ የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የሴቶች ማኅበር፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ እና የምገባ ኤጀንሲ ናቸው፡፡
ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመከላከያ ሚኒስቴር ያስረከቡ ሲሆን÷ በመዲናዋ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የተለያዩ አካላት የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመተውን የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉት የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የሴቶች ማኅበርና የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በጋራ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የምገባ ኤጀንሲ ደግሞ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እንዲሁም በተማሪዎች ምገባ ስራ የተሰማሩ እናቶች ከደመወዛቸው 500 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡

በሌላ በኩል የጅማ ዞን የማና ወረዳ ቄሮና ቀሬዎች 4 ሚሊየን ብርና 66 በሬዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

ከድጋፉ በተጨማሪ የወረዳው ቄሮዎች፥ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይን ዱካ በመከተል መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል መመዝገባቸው ተገልጿል።

ወጣቶቹ “ከዚህ ቀደም መንገድ ዘግተን ወያኔን ከስልጣን እንዳስወገድነው ሁሉ፥ አሁንም ከወረረው መሬት ንብረት ዘርፎ እንዳይወጣ ግብዓተ መረቱትን እንደሚፈፅማለን” ብለዋል።

የማና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፈድሉ ዛኪር፥ መከላከያን ለመደገፍ የወረዳው ወጣቶች ጋ ያለው ተነሳሽነት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፥ በርካታ ወጣቶች ግንባር ድረስ ለመዝመት ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልፀዋል።

በድጋፍ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የጅማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ የሱፍ ሻሮ በበኩላቸው፥ በአጠቃላይ የዞኑ ነዋሪዎች ለሰራዊቱ 136 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንና የወጣቶች አስተዋፆም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል።

በሙክታር ጠሃ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.