በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ዓለም ዓቀፉን የ #በቃ ንቅናቄ ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች የምእራባውያንን ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን በማለት አለም አቀፉን የ #በቃ ንቅናቄ ተቀላቀሉ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑ ከ7ኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪወች በአደባባይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡
በሰልፉ አሜሪካ በዴሞክራሲ ሰበብ አሸባሪን አትደግፊ፣ አሜሪካ የአማራን ዘር ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለሽን ሴራ አስወግጅ፣ ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ የምእራባውያን ጣልቃ ገብነት ይቁም፣እኛ ኢትዮጵያውያን ስለራሳችን እኛ እናውቃለን፣ ምእራባውያን እጃችሁን አንሱ የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡
አባቶቻችን የውጭ ጣልቃ ገብነትን ተቋቁመው ያስረከቡን ነጻነት በእኛ ዘመን አይደበዝዝም ብለዋል በሰልፉ የተሳተፉ ተማሪዎች፡፡
ተማሪወቹ ሀገር ለመለወጥ ተግተን መሥራት፣ አዲስ አስተሳሰብና ችግር ፈች ብልሀት አመንጭ መሆን አለብንም ነው ያሉት፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀይለ ማርያም እሸቴ ÷ አሜሪካ ጣልቃ ገብታ ያፈረሰቻቸው ሀገራት ዜጎች ለኛ ትምህርት ናቸው፤ ጠንካራ መሪና ሀገር ወዳድ ዜጎች ነን፤ ለምዕራባውያን ሴራ አንንበረከክም ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ÷ ሀገራችንን የምንጠብቃት እኛ ነን፤ የምእራባውያን ሚድያ እና ልኡካን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚገቡበት ጊዜ አብቅቷል ብለዋል፡፡
በአለባቸው አባተ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!