መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት በትኩረት እየሰራ ነው – አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የለውጡ መንግሥት የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራው ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ገለጹ።
የዓለም የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም ለ30ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል፡፡
የአካል ጉዳተኞችን መሪነትና ተሳትፎ በማረጋገጥ አካታች፣ ተደራሽና ዘላቂ ድህረ ኮቪድ19 ዓለም እንገንባ በሚል መሪ ቃል ነው ቀኑ የተከበረው፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ በዓሉ ኢትዮጵያ በህልውና ዘመቻ ላይ ሆና ያከበረችው በመሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡
የዘንድሮ የአካል ጉዳተኞች ቀን ሲከበር ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው የዓለምና የአገር አቀፍ አዋጆች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ መጣር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ በበኩላቸው÷ የለውጡ መንግሥት የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራው ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
የበዓሉ ተሳታፊ አካል ጉዳተኞችም ጀግናውን የአገር መከላከያ ሠራዊት ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
አሸባሪው ህወሓት 27 ዓመት ሙሉ አፋኝ ሕጎችን በማውጣት አካል ጉዳተኞችን መፈናፈኛ ሲያሳጣ እንደነበር አስታውሰዋል።
ህወሓት ለራሱ የሚበጀውን አዋጅ በማውጣት ጉዳት የደረሰባቸውን የራሱን ወገኖች ተጠቃሚ ሲያደርግ መቆየቱንም አብራርተዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!