በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ተማሪዎችን ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተቀበለ
አዲስ አበባ ፣ህዳር 27፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከ780 በላይ ተማሪዎችን ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል።
ተማሪዎቹ በአክሱም፣ መቀሌ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በቅበላ ዝግጅቱ ላይ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሰ ሀብታሙ እና የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ የተገኙ ሲሆን÷ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ፎረም አባላት በጋራ በመሆን ተማሪዎቹ በሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ከጎናቸው በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ያቋጡትን ትምህርት መቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!