Fana: At a Speed of Life!

ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን በፈጸመው አሸባሪው ህወሃት ላይ ማዕቀብ እንዲጣልበት ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሃት በፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ማዕቀብ እንዲጣልበት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ተጻፈ፡፡
አሸባሪው ህወሃት በፈጸመውና እየፈጸመ ለሚገኘው ከባድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ማዕቀብ እንዲጣልበት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ተጻፈ።
አሜሪካ በሽብር ቡድኑ ላይ በአስቸኳይ ማዕቀቡን ተግባራዊ እንድታደርግ የጠየቀው በአሜሪካ የኢትዮጵያዊያን ፐብሊክ ጉዳዮች ኮሚቴ ነው።
ኮሚቴው ጥያቄውን ያቀረበው ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋዊ ደብዳቤ በመጻፍ ነው፡፡
ኮሚቴው ለሚኒስቴሩ ደብዳቤውን ለማጻፍም የተገደደው ህወሓት በፈጸመውና እየፈጸመ በሚገኝ ከባድ ኢ- ሰባአዊ ድርጊት ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡
ኮሜቴው በደብዳቤው “በአሸባሪው ህወሓት ላይ በአሜሪካ መንግስት ሊጣሉ የታሰቡት ማዕቀቦች በአፋጣኝ እንዲተገበሩ በአክብሮት እንጠይቃለን” ብሏል፡፡
በግልጽ እንደሚታወቀው ብዙ የአሸባሪው ህወሓት አመራር አባላት ከፍተኛ ሃብትና ካፒታል በውጭ አገር አላቸው ያለው ኮሚቴው ሆኖም አሜሪካም ሆኑ ሌሎች የአለም ማህበረሰብ አባላት በአሸባሪው ህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ አልተገበሩም ነው ያለው።
በእነዚህ ግለሰቦች እና ድርጅቱ ላይ ማዕቀብ መጣል፤ በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊትን በመከላከል ንጹሃንን ከአሰቃቂ ጥቃት መታደግ ይቻላል ሲል አስረድቷል፡፡
አሜሪካ ከዚህም በተጨማሪም ወቅታዊ የኢትዮጵያን ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋን እንድታራምድ ነው የኢትዮጵያዊያን ፐብሊክ ጉዳዮች ኮሚቴ የጠየቀው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.