Fana: At a Speed of Life!

በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው የኤሌክትሪክ መስመር የመጠገን ሥራ ይከናወናል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ ቀናት ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው የኤሌክትሪክ መስመር የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

እንዲሁም በሽብርተኛው ህወሃት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ከሸዋ ሮቢት እስከ ካራቆሬ ባሉት ከተሞች የሚገኙ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተጠግነው መጠናቀቃቸው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሸዋሮቢት፣ በጀውሃ፣ በሰንበቴ፣ በአጣዬና ካራቆሬ ከተሞች የሚያልፈውን የከፍተኛ መስመር በመጠገን ለስርጭት መስመሮች ኃይል መስጠት እንዲችሉ የዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጀመረው የሥርጭት መስመሮች የጥገና ሥራ እንደተጠናቀቀ የተጠቀሱት ከተሞችና አጎራባች የገጠር ቀበሌዎች በፍጥነት የኤሌክትሪክ ሀይል ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀጣዮቹ ቀናትም ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመርን የመጠገን ሥራ እንደሚሰራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.