Fana: At a Speed of Life!

የሸኔ የጥፋት ቡድን በፀጥታ ሀይሎች ጥምረት እየተደመሰሰ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን ለማፈራረስ ከህወሓት አሸባሪ ቡድን ጋር በጥምረት እየሰራ የሚገኘው የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ ቢገኝም በፀጥታ ኃይሎች ጥምረት ህልሙ እየከሸፈ ይገኛል።

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ ጉጂ ነገሌ ቦረና እና በአርሲ ነገሌ አካባቢ ሽብር ለመፍጠር አስቦ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሸኔ ቡድን ላይ የማያዳግም ርምጃ ተወስዶበታል፡፡

የአካባቢውን ሰላም ለማወክ አቅዶ በተንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና ኦሮሚያ ልዩ ሀይል በጥምረት ባደረጉት ኦፕሬሽን ከፍሉ ሲደመሰስ ከፊሉ ቁሰለኛና ምርኮኛ ሆኗል።

የፀጥታ ኃይሎች ጥምረት በአሸባሪው ሸኔ ላይ የጀመሩትን  ጥቃት አጠናክረው ይቀጥላሉ ትብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.