አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ፈጽሟል
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በወረራ ይዞ በቆየባቸው አካባቢዎች በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የአፋር ልማት ማህበር አስታወቀ፡፡
ከተመሰረተ 10 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፋር ልማት ማህበር በዋናነት የክልሉን ነዋሪዎች ህይወት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ነው የተባለዉ፡፡
ማህበሩ በተለይ በክልሉ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትንና ሌሎች መሰረት ልማቶችን ማስገንባቱን የማህበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን ሳዲቅ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ማህበሩ ያስገነባቸውን ጨምሮ በርካታ ትምህርት ቤቶችን ማውደሙን ነው የተናገሩት፡፡
የጤና ተቋማትን ማውደሙንና የመንገድ ፕሮጀክት ቁሳቁሶችን እንደዘረፈ ገልጸዉ÷አሸባሪ ቡድኑ ያወደማቸውን ሃብቶች መልሶ ለማቋቋም በርካታ ገንዘብ እንደሚጠይቅም ነው ያነሱት፡፡
ማህበሩ በቅርቡ የወደሙ ንብረቶችን የሚመለከት ጥናት እንደሚያከናውን ጠቅሰው÷በጥናቱ መሰረት መልሶ የማቋቋም ስራው እንደሚጀመር አውስተዋል፡፡
ማህበሩ ያሉትን አቅሞች በሙሉ በመጠቀም ተቋማቱን ወደ ስራ ለማስገባት እንደሚንቀሳቀስም ጨምሮ ገልጸዋል፡፡
ከማህበሩ አቅም በላይ የሆኑትን ደግሞ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለማሟላት እንደሚሰራም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙም ማህበሩ ጥሪ ማቅረባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!