አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን እና በዚምባብዌ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት እና በሌሎች የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፈነቶች ያገለገሉት አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ በ1946 ዓ.ም በሐረር ከተማ ልዩ ስሙ ሸንኮር በተባለ ቦታ ከአባታቸው አቶ ዶላል መሐመድ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አሚና አብዲ ተወለዱ።
አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ተከታትለው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በከፍተኛ ውጤት ከተመረቁ በኃላ በመምህርነት፣ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት በሬዲዮ ፕሮግራም አስተባባሪነት፣ በሱማሌ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊነት እንዲሁም በክልሉ የቀይ መስቀል ቦርድ ሊቀ-መንበርነት እንዲሁም በ1992 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን በህዝብ ተወካይነት አገልግለዋል።
አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ በየመን እና ዚምባብዌ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነትን ሀገራቸውን በቅንነት እና በታታሪነት ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል።
አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ ባደረባቸው ህመም በአገር ውስጥና በውጭ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይዋል።
አምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ የስድስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ።
የኢ.ፌ.ዲ.ዲ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአምባሳደር አብዲ ዶላል መሐመድ ህልፈተህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ፣ ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!