Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ የትምህርት ተቋማት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞንና የመራዊ ከተማ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የጎንደር ጎቶኒያል ኮሌጅ የትምህርት ማህበረሰብ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ ናቸው፡፡
የሰሜን ሸዋ የዞኑ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጀ ሰማ ÷ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ የሚገኙት በዞኑ የሚገኙ 52 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።
ተማሪዎቹ÷ ተምሮ ትልቅ ደረጃ መድረስ የሚቻለው አገር ሰላም ስትሆን በመሆኑ የአገር ሰላም እስኪረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የመራዊ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን የዘማች አርሶ አደር የደረሰ ሰብልን መሰብሰባቸውን ከአማራ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የጎንደር ጎቶኒያል ኮሌጅ ተማሪዎችና የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ የባህርዳር ፖሊ ቴክኒክ የትምህርት ማህበረሰብ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች ፣በደቡብ ጎንደርና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ለሚገኙ የዘማች ቤተሰቦች ሰብል እየሰበሰቡ መሆኑን ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኘው ፀሐይ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኔን ሰራተኞች፣ አባላትና አመራሮች የዘማች ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል ሰብስበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.