የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቋሙን በመከላከል መስዋዕትነት ለከፈሉ ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነሐሴ 6 2013 ዓ/ም የህወሓት የሽብር ቡድን ወደ ጋይንት ሰርጎ በመግባት ነፋስ መውጫ ከተማ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ለመዝረፍ ሙከራ ሲያደርግ የባንኩ ጠባቂዎች የነበሩት ብርቱ ትግል አድርገዋል።
በወቅቱ የባንኩ ጠባቂ የነበሩት አቶ ዘውዱ ንጋቴ እና ወታደር ማሬ ይርሳው የሽብር ቡድኑን አናስገባም በማለት ከፍተኛ ትግል በማድረግ እስከ መጨረሻው በመዋጋት የህይወት መስዋትነት እና የአካል ጉዳት ከፍለዋል።
በነበረው ፍልሚያ አቶ ዘውዱ ንጋቴ ህይወታቸው ሲያልፍ ፥ ወታደር ማሬ ይርሳው የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል።
የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ የጎንደር ዲስትሪክት አገሬን እና መስሪያ ቤቴን አላስደፍርም ብለው የህይወት እና የአካል መስዋዕትነት ለከፈሉ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው የምስጋና እና የድጋፍ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ደመዎዜ ባልቤ፥ ነፋስ መውጫ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ሰጥተዋል።
በዚህም ህይወታቸው ላለፈው ለአቶ ዘውዱ ንጋቴ ባለቤት ለወ/ሮ ሽንብራ አለነ 150 ሺህ ብር ሲያበረከትላቸው ፥ ሁለት ልጆቻው ደግሞ በባንኩ ቋሚ ሰራተኛ ሆነው እንዲቀጠሩ ተወስኗል።
የመቁሰል አደጋ ለገጠማቸው የባንኩ ጥበቃ ደግሞ ከዚህ በፊት በኮንትራት የነበረውን በቋሚነት እንዲቀጠር ተወስኗል።
በምንይችል እዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!