Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ዞን ለሰራዊቱ ከ179 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ዞን ለመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ179 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
 
የወላይታ ዞን ሴቶች አደረጃጃት ከዞን፣ ከከተማ አስተዳደር እና ከወረዳ ጋር በመተባበር ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ዛሬ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
ነዋሪዎች በደጀንነት ለሰጡት ድጋፍ ፣ አመራሮችና ሌሎች አካላት ህዝቡን አስተባብረው ላበረከቱት አስተዋጽኦ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በህዝቡ ድጋፍ ትግሉን በግንባር ላይ ሆኖ በተጨባጭ እየተፋለመ ያለው ጀግና ሠራዊታችን የአሸባሪውን ህወሃት ቡድን እኩይ ተግባር መመከት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
በአሸባሪው ቡድን እጅ የተያዙ አከባቢዎች ነጻ መውጣት የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ርብርብ ውጤት እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
 
በአማራና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎቻችን መልሶ የማቋቋምና የመደገፍ የኢትዮጵያውያን ባህል እንደሆነ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸው፥ ድጋፉም ከሁሉም አካላት እንደሚጠበቅም ነው ያመለከቱት፡፡
 
የዞኑ ህዝብ እስከ አምስተኛ ዙር ድረስ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከ179 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማደረጉን የወላይታ ዞን የሀብት አሰባሰብ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም አብራርተዋል፡፡
 
የወላይታ ዞን ሴቶች አደረጃጃት ከዞን፣ ከከተማ አስተዳደርና ከወረዳ ጋር በመተባበር 1 ሺህ 725 ኩንታል በሶ፣ 262 ኩንታል ስኳር፣ 2 ኩንታል ቆሎና 605 ዩኒት ደም በአጠቃላይ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ማዘጋጀቱን ወ/ሮ እታገኝ አስታውቀዋል፡፡
 
በማቱሳላ ማቴዎስ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.