Fana: At a Speed of Life!

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከእቅድ በላይ አሳክቷል- የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ባለፉት አምስት ወራት የእቅዳቸውን 120 በመቶ ማሳካታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ በሞጆ እና አዳማ የሚገኙ የቆዳ እና የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን የጎበኙ ሲሆን÷ባለፉት አምስት ወራት 80 የሚደርሱ መካከለኛና ከፍተኛ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
ይህም በቀጣይ የተሻለ ስራ ቢሰራ የአገርን ኢኮኖሚ የመደገፍ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ኢንዱስትሪው ለአገር ኢኮኖሚ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጠናከር መንግስት በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑን ጠቅሰዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማም የግል ተቋማትን በቅርበት ለመደገፍና ለማበረታት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ÷የኢንዱስትሪ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይም የቆዳና ቆዳ ውጤቶችን ምርት ለማሳደግ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ በአገሪቱ 27 የሚደርሱ መካከለኛና ከፍተኛ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡
ከእነዚህም 19 የሚሆኑት የተሻለ ምርት በማምረት ላይ እንደሚገኙ እና በአገሪቱ ከሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች 90 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ገልጸው÷ ባለፉት አምስት ወራት የእቅዱን 73 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.