Fana: At a Speed of Life!

የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ላይ ያደረሰው ጉዳት ግቡ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ያሳያል-ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ህወሓት በፈፀመው ወራረ ምክንያት የወደሙ የመንግስትና የግል ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊትና በህዝቡ መሰረታዊ ጥቅሞች ላይ ያደረሰው ጉዳት የሽብር ቡድኑ አልፋና ኦሜጋ ግቡ ኢትዮጵያን ማፍረስ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የመልሶ ግንባታ ስራ ለመጀመር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ዶክተር ይልቃል አስረድተዋል፡፡

የህወሓት የሽብር ቡድን እስኪደመሰስ ድረስ ሁሉም የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

ህብረተሰቡ የሽብር ቡድኑ ዘርፎና ደፍሮ እንዳይወጣ ለአካባቢው የሰላም ዘብ መሆን እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወጣቶች መከላከያን በመቀላቀል የተደቀነውን የሕልውና አደጋ እንዲቀለብሱ ጥሪ ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.