Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ጀማል ከባህሬን የነዳጅ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አምባሳደር ጀማል በከር ከባህሬን የነዳጅ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ጋር በሁለትዮሽ እንዲሁም በባለ ብዙ ወገን ቀጠናዊ ግንኙነቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር በሀገራችን ባለው አጠቃላይ የሠላምና የጸጥታ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የባህሬን የነዳጅ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ በበኩላቸው ÷ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው ኢትዮጵያ ቀደምት የስልጣኔ እና የነጻነት ሀገር እንደሆነች አንስተዋል።

በቀጣይም ዘርፈ ብዙ ዕድሎች እንዳላት መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅሀፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

በሌላ በኩል ሀገራቸው በብረት ማዕድን፣ ኮባልትና በአሉሙኒየም በማምረቻው ዘርፍ በአገራችን መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላት አመላክተዋል፡፡

በውይታቸው ሀገራቱ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ላይ የበለጠ በጋራ ለመስራት እና ለማጠናከር ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.