ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከጋቦን ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከጋቦን ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ እና ከአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ስላለው የህልዉና ማስከበር ዘመቻና በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
ጋቦን በሚቀጥለው ወር የፀጥታው ም/ቤት ተለዋጭ አባል እንደምትሆን ይታወቃል።
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ በአፍሪካ ሀገራት ያደረጉትን የስራ ጉብኝት በጋቦን ማጠናቀቃቸውን ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኮቲዲቯር ፕሬዝዳንት፣ ከኢትዮጵያውያን ማህበረስብ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!