አሜሪካ በዊክሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ ላይ የመሰረተችው ክስ የዓለም የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን የሚጎዳ ነው- ሰቴላ ሞሪስ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ዩናይትድ ስቴትስ በዊክሊክስ መስራች ጋዜጠኛ ጁሊያን አሳንጅ ላይ የመሰረተችው ክስ የአለም የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን የሚጎዳ ነው ስትል የቅርብ ጓደኛዉ ሰቴላ ሞሪስ ተናገረች።
አውስትራሊያዊ ጋዜጠኛ፣ አርታኢ፣ አሳታሚ እና የዊክሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በዩኤስ ጦር የሲ አይ ኤን የስለላ አካሄድ በተመለከተ ተከታታይ ትንተናዎችን በመስጠት ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ ጋዜጠኛዉ ሚሰጥራዊ መረጃዎችን አውጥቷል በሚል የአሜሪካ መንግስት ጋዜጠኛዉ እንዲታሰር እና እንዲሰቃይ ከማድርግ በተጨማሪ ለአንባቢያን በሚያበቃዉ የህትመት ጋዜጣ ድርጅቱ እና ግለሰቡ ላይ ክስ መስርቷል፡፡
ይህን አስመልክቶ ከሲጅቲ ኤን ጋር ቆይታ ያደረገቸዉ የቅርብ ጓደኛው ስቴላ ሞሪስ እንደተናገረችው፥ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በጋዜጠኛው ላይ የመሰረተው ክስ በዓለም ዙሪያ ያለውን የፕሬስ ነጻነት የሚጎዳ ነው ስትል ተናግራለች፡፡
ጋዜጠኛው አሜሪካ በተለያዩ ሃገራት የምትፈፅማቸውን አሻጥሮችና የጦር ወንጀሎችን ሲተነትን እንደነበር የምትናገረው ስቴላ ሞሪስ ሃገሪቱ በጋዜጠኛው ላይ የመሰረተችዉ ክስ በአለም ላይ ያለዉን የመገናኛ ብዙህን የዘገባ ነጻነት ተፅዕኖ ውስጥ የሚከት መሆኑንም ተናግራለች፡፡
ጋዜጠኛ ጁሊያን አሳንጂ ከዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጊዜ ጀምሮ ሰባት አመታትን በእስር ቤት አሳልፏል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!