ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ ዛሬ ተጀምሯል ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በመድረኩ ተገኝተዋል።
መድረኩ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ነው የተገለፀው ።
ጥቅምት ወር ላይ ባህር ዳር በተካሄደው የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች መድረከ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ይገመግማል ።
እንደዚሁም ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
በአልአዛር ታደለ