ሊቀ ጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስና የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡
ዴዝሞንድ ቱቱ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓትን ለማስወገድ ባደረጉት ትግል በፈረንጆቹ በ1984 የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
በዚህም ከደቡብ አፍሪካ አልፎ በመላው ዓለም አድናቆትን እና ታዋቂነትን አትርፈዋል፡፡
የሊቀ ጳጳሱ ህልፈት ምክንያት እስካሁን በዝርዝር አለመታወቁንም ቲ አር ቲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!