Fana: At a Speed of Life!

የአየር ንብረት ለውጥ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ማፈናቀሉን የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2021 የዓለም አየርንብረት ለውጥ ያስከተለው አደጋ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡
በፈረንጆች 2021 የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተላቸው አስር አስከፊ ክስተቶች ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት ገልጿል፡፡
በዚህ ሳቢያም የ170 ቢሊየን ዶላር ጉዳት ደርሷል ነው ያለው ዘገባው።
አብዛኛዎቹ የዋጋ ግምቶች በኢንሹራንስ ወጪ ላይ ብቻ መሰረት ተደርገው የተሰሉ በመሆናቸው ትክክለኛው ወጪ ከዚህም ሊዘል እንደሚችል ዘገባው አመላክቷል፡፡
በነሀሴ ወር አሜሪካን የመታው “አይዳ” የተባለው አውሎ ንፋስ 65 ቢሊየን ዶላር ወጪ ያስወጣ ሲሆን የ95 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፤ በሰኔ ወር በአውሮፓ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ 240 ሰዎች ለህልፈት ዳርጎ 43 ቢሊየን ዶላር ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ አስከትሏል ነው ያለው።
በተመሳሳይ በቻይና ሄናን ግዛት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 320 ዜጎችን ለሞት፣ ከአንድ ሚሊየን በላይ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ መዳረጉም ነው የተጠቀሰው።
የጎርፍ አደጋው ለ17 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ውድመት መሆኑንም የአናዶሉ ዘገባ ያመላክታል።
ሪፖርቱ ያተኮረው በበለጸጉ ሃገራት ላይ ያስከተለው ውድመት ላይ ቢሆንም ችግሩ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ብዙም ተጽእኖ የሌላቸው ድሃ ሀገራትንም የጥቃቱ ሰለባ አድርጓል ነው የተባለው፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.