Fana: At a Speed of Life!

ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እቅዶች ላይ መልካም አፈጻጸም መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አዳዲስ የታክስ መሠረት ማስፋት፣ የበጀት ጉድለት፣ የፕሮጀክቶች ክትትልን ጨምሮ ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ላይ መልካም አፈጻጸም መመዝገቡን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ተናገሩ።
 
የገንዘብ ሚኒስቴር የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፥ የሃገር ውስጥ ገቢ፣ አዳዲስ የታክስ መሠረት ማስፋት፣ የበጀት ጉድለት እና የፕሮጀክቶች ክትትል ላይ መልካም አፈፃፀም መመዝገቡን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
 
የገንዘብ ሚኒስቴር ላይ በተካሄደው ግምገማ ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ምላሽ ሰጥተዋል።
 
የሀገር በቀል ሪፎርም፣ ክልሎች ሀገራዊ ገቢ አሰባሰብ ላይ መልካም አፈፃፀም እየታየ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.