አየር መንገዱ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደ ላሊበላ የቀጥታ በረራ ይጀምራል
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደ ላሊበላ የቀጥታ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
አየር መንገዱ በረራውን በየቀኑ እንደሚያካሂድም ነው ያስታወቀው።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በላሊበላ ከተማ በፈጸመው ወረራ በከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱ የሚታወስ ነው።
ከተማዋ ከአሸባሪ ቡድኑ ነጻ ብትወጣም በደረሰው ጉዳት ምክንያት የአውሮፕላን በረራ ሳይጀመር ቆይቷል።
የላሊበላ ከተማ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ጎብኚዎች የምትዘወተርና ከቱሪስት መዳረሻ ከተማዎች መካከል አንዷ ናት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!