ዳያስፓራዎች በአፋር ዱብቲ የበጋ መስኖ ስንዴን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር የመጡት ዳያስፓራዎች በአፋር እያደረጉት ባለው ቆይታ በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ 500 ሄክታር ላይ እየለማ ያለ እርሻን ተመልክተዋል።
ቦታው ቀደም ሲል የተንዳሆ ስኳር ልማት የሸንኮራ እርሻ ቦታ የነበረ ሲሆን፥በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ተገቢውን ጥቅም ሳይሰጥ መቆየቱ ተነግሯል።
የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አብዱ ኢበራሂም÷የበጋ መስኖው በልማት ግንባር ለማሸነፍ እያደረግነው ያለው ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል፡፤
በለማው የበጋ መስኖ ስንዴ በሄክታር ከ30 እስከ 35 ኩንታል ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆሙት ሃላፊው፥ እንደ ክልል 10 ሺህ ሄክታር ለማልማት መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡
በጉብኝት መርሃ ግብሩ ለዳያስፓራዎቹ በዘርፉ በሚስተዋሉ ችግርች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!