ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተሰጣቸው።


ዛሬ በተካሄደ ስነስርዓት ፥ ውጊያ ለመሩ ፣ ሀይል ለመሩ ፣ ድልና ውጤት ላስገኙ ከፍተኛ የጦሩ መኮንኖች በየደረጃው የማዕረግ ዕድገት ተሰጥቷል።
በዚህም መሰረት 1 የፍልድ ማርሻል ማዕረግ ፣ 4 የሙሉ ጀነራል ማዕረግ ፣ 14 የሌተናል ጀነራል ማዕረግ፣ 24 የሜጀር ጀነራል ማዕረግ እና 58 የብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ ተሰጥቷል።
የጀነራል መኮንኖቹ ሹመት በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር አብይ አሕመድ አቅራቢነት በርዕሰ ብሄር ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ነው የተሰጠው።
በዓላዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!