ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የህግ የበላይነትን የማስከበር ክንውኑ የሚገኝበትን ደረጃ እንዲሁም መንግስት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ለጆ ባይደን ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በቅርቡ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሚደረገውን መልሶ የመገንባት ርብርብ አስመልክቶ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት አስረድተዋል።
ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነትም አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!