Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ግጭቶችን የመፍታት እና የማርገብ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ባለፉት ሦስት ዓመታት ግጭት ለመፍታት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት፣ የሽግግር ፍትሕ ለመስጠት፣ የሕዝቡን አብሮነት ለማጠናከር እና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ መቆቱን ገልጿል፡፡
 
ኮሚሽኑ የሦስት ዓመታት እንቅስቃሴውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን÷ ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራትና እስከ ክልል ድረስ ጽህፈት ቤቶችን በመክፈት በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ግጭቶችን የመፍታት እና የማርገብ እንቅስቃሴዎች ጀምሬያለሁ ነው ያለው፡፡
 
ስራው ለሀገራችን አዲስ እንደመሆኑ መጠን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር ስለ ሰላም እና ዕርቅ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መስራቱን አስታውቋል፡፡
 
በሦስቱ ዓመታት ውስጥ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችም የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም እና ከባለድርሻዎች ጋር በመተባበር መፍታት መቻሉን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ኮሚሽኑ በቀጣይም የሥራ ዘመኑ ተራዝሞለትና የሕግ ክፍተቶቹ ተቀርፈውለት ስራውን በተሻለ ይሰራ ዘንድ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግለት ሕዝብ እና መንግሥትን ጠይቋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.