የዳያስፖራ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ወንጂ የበጋ የመስኖ ስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራ አባላት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ወንጂ በአዳማ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳ እየጎበኙ ነው፡፡
የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ፥በጉብኝቱ ላይ ለተሳተፉ ዳያስፖራዎች የበጋ የመስኖ ስንዴ፣ አቮካዶ፣ ፓፓያ እና ሌሎች ምርቶች ላይ እየተገኘ ያለውን ውጤት አብራርተዋል።
ዳያስፖራው በዲፕሎማሲው ለሃገሩ እየሞገተ ከሚያመጣው ውጤታማ ስራ ጎን ለጎን በሃገሩ የልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ተጠይቀዋል።
በሃገር ውስጥ እየጨመረ የመጣውን ምርታማነት ዳያስፖራው እንዲደግፍ እና የኢትዮዽያን እድገት ለማረጋገጥ በጋራ እንዲቆም ምቹ አሰራሮች መዘርጋታቸውን አቶ ጌቱ ገልጸዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ ዳያስፖራዎች የተመለከቱት ውጤታማ የምርት ዝግጅት እና አፈጻጸም የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጉብኝቱ ዳያስፖራውን በሃገር ውስጥ እንዲያመርት አይን ከፋች መሆኑንም ገልጸዋል።
በፍሬህይወት ሰፊ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!