Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ባህላዊ ስፖርት ሻምፒዮና በሰንዳፋ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ10 ቀናት የሚቆይ የኦሮሚያ ባህላዊ ስፖርት ፌስቲቫል በሰንዳፋ ከተማ መጀመሩን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ 27ኛው የባህላዊ ስፖርት ሻምፒዮና እና 12ኛው የባህል ፌስቲቫል በተለያዩ ስፖርታዊ መርሀ ግብሮች እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሳሚያ አብደላ የገለጹት፡፡

በዘንድሮው የባህላዊ ስፖርት ሻምፒዮና 21 የኦሮሚያ ዞኖችና 18 ከተሞች እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው፡፡

የባህላዊ ስፖርት ውድድሩ እና ፌስቲቫሉ ባህልን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚያግዝም የሰንዳፋ ከተማ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.