Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ እንደ አዲስ አገርሽቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በትናንትናው እለት በሱዳን አዲስ ዙር የሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ ተገለፀ፡፡

የካርቱም መንትያ ከተማ በሆነችዉ ኦምዱርማን በትላንትናው እለት በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ወደ ጎዳና በመውጣት በሱዳን ወታደራዊ መንግስት ላይ ያላቸዉን ተቃውሞ በሰልፍ ገልፀዋል።

የተቃውሞ ሰልፉ በአልበሽር ላይ ለተነሳው ህዝባዊ አመጽ ከፍተኛ ሚና በነበረው የሱዳን ባለሙያዎች ማህበር እና የተቃዋሚ ኮሚቴዎች የተጠራ ስለመሆኑም ተገልጿል።

የሱዳን የፀጥታ ሀይሎች ሰልፈኞቹ ወደ ሰፈራቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ ቢሰጡም ሰልፈኞቹ የፀጥታ ሀይሎችን ትዕዛዝ አለመቀበላቸው የተገለጸ ሲሆን÷ ሰልፉን ለመበተን በተደረገ ሙከራ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የሰልፈኞቹ የህክምና ቡድን አስታውቋል።

ሰልፈኞቹ ፀረ መፈንቅለ መንግስት መፈክሮችን ያሰሙ ሲሆን÷ በተጨማሪም ቀደም ሲል በነበሩ ሰላማዊ ሰልፎች የተገደሉ ሱዳናውያንን ፎቶ በመያዝ ተቃውሟቸውን ማሳማታቸውን አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.