Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ያደረገችው አደገኛ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አሜሪካን አስቆጣ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አደገኛ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ አሜሪካ አስቸኳይ ንግግር ማድረግ እንደምትፈልግ አስታውቃለች፡፡

ዋሽንግተን ፒዮንግያንግ መካከለኛ ርቀት ያለው ባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ህዋ ካስወነጨፈች በኋላ የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና ሚሳኤል ፕሮግራሞች እጅግ እንዳሳሰቧት ገልጻለች፡፡

ስለሆነም በጉዳዩ ዙሪያ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በአስቸኳይ መነጋገር እንደምትፈልግ ነው ያሳሰበችው፡፡

አንድ የባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን እንደተናገሩት÷ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ከበድ ያሉ ውይይቶችን ማድረግ አለብን ብለን እናምናለን ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዘመን ከሰሜን ኮሪያ ጋር ለመነጋገር ደጋግማ ብትፈልግም ውጤታማ መሆን እንዳልቻለች ዘገባው አመላክቷል ፡፡

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ሶስት ጊዜ ስብሰባዎችን ቢያደርጉም ውይይቱ ግን በፒዮንግያንግ የተጣለውን ማዕቀብ ማስነሳትን ያገናዘበ አልነበረም ነው የተባለው ።

ባለስልጣኑ ይህ የሰሜን ኮሪያው አደገኛ የሚሳኤል ሙከራ ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ህጎችን እንደማታከብር እና የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን እየጣሰች እንደሆነ ማሳያ ነው ማለታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል ፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.