Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፍ ገበያ የኢትዮጵያ ቦንድ ሽያጭ መሻሻል አሳየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በዓለም ገበያ የኢትዮጵያ የውጭ ቦንድ ሽያጭ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱ ተገለጸ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈፃፀም ጊዜ እንዲያጥር ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ የዶላር ቦንድ አፈፃፀም የቦንድ ሽያጩ በዶላር 6 ሳንቲም የፍላጎት ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ የውጭ ቦንድ ሽያጭ በ13 በመቶ የአፈጻጸም ዕድገት ማሳየቱ ከ80 በማደግ ላይ ካሉ ሀገሮች አንጻር የተሻለ መሆኑን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጸጥታ ችግር ምክንያት የቦንድ ሽያጩ ቀንሶ እንደነበርም አስታውሷል።

የውጭ ቦንድ በዓለም ላይ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት የሚቀርብና በምትኩ ወለድ ታስቦ የሚከፈልበት ሰነድ ሲሆን ቦንድ ለሽያጭ የሚቀርበው የውጪ ምንዛሬ ክፍተትን ለመሙላት፣ የቆዩ የውጪ እዳዎችን በአፋጣኝ ለመክፈል፣ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት መሆኑን መረጃዎች እንደሚያሳዩ ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.