Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ዕዝ በተለያዩ ዘመቻዎች ድጋፍ ላደረጉ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ዕዝ በህግ ማስከበር፥ በህልውና እና በህብረ ብሔራዊ ለአንድነት ዘመቻዎች ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎች የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

ዕዙ ባዘጋጀው የሽልማት ሥነ-ስርዓት እውቅና የተሰጣቸው የአፋር ክልል፣ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፣ የእስልምና ጉዳዮች ፣ የሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ፣ ራያ ቆቦ፣ ሀብሩ ወረዳ እና ሌሎች መስተዳድሮችም የተዘጋጀላቸውን የምስክር ወረቀት እና የዋንጫ ሽልማት ከሌ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ እጅ ተቀብለዋል።

ጄኔራል መኮንኑ ፥ ‘‘አሸባሪውን ኃይል ለመደምሰስ በተደረገው ትግል ለሠራዊታችን ያደረጋችሁት መስዋዕትነት እስከ መክፈል የደረሰ ጀግንነት ምስጋና ይገባችኋል’’ ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን መስተዳድር በበኩሉ ፣ ዕዙ ባካሄደው የጀግና ሜዳይ አሰጣጥ ሥርዓት ላይ ለተገኙ የክብር እንግዶች ለጄኔራልና ለሌሎች ከፍተኛ መኮንኖች የራያ የባህል ልብስ ስጦታ አበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ ከተበረከተላቸው መካከል በቆቦ ወረዳ የጉራ ወርቄ ቀበሌ ህዝባዊ ሚሊሻዎች ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ባደረጉት ውጊያ አካባቢያቸውን ያላስደፈሩ ጀግኖች መሆናቸው ተገልጿል።

የወርቄ ቀበሌ አባ-ሀጋ በካሪስ ጎቤ የተሰጠን እውቅና በቀጣይም ከሰራዊታችን ጎን ተሰልፈን አሸባሪውን ለመደምሰስ የሞራል ድጋፍ ይሆነናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.