ቱኒዚያ፣ የማዳጋስካር እና የኬፕ ቨርዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦተማን ጃርዲ፣ የማዳጋስካር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖትሪክ ራአጆልንት እንዲሁም የኬፕ ቨርዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያና ዳጃምላ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና በ40ኛዉ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ለመሳተፍ ሌሊቱን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሮቹ በቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጉዳዮች ዋና ሹም አምባሳደር ምህረተዓብ ሙሉጌታ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!