አቶ ደመቀ መኮንን ከተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከ40ኛው የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ከቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ጄራንዴ ጋር በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያን እና ሞሮኮን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከሞሮኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሞሮኮ ከግብርና እና ቱሪዝም ዘርፎች በተጨማሪ በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱ ከ40ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡