Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አገራት መሪዎች ለህብረቱ ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ አገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት ጠዋት የሞሪታንያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ኡልድ ኤል-ጋዝዋኒ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ምባንጎ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ምባንጎ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የሲሼልሱ ፕሬዚዳንት ዋቨል ራምካላን በመሪዎቹ ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የግብርና ሚኒትር አቶ ኡመር ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ኮትዲቯርና ማላዊ ፕሬዚዳንቶች እንደዚሁም የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ለህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

በበርናባስ ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.