የቻይና እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በቤጂንግ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር በቤጂንግ ተገናኝተው ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡
በሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተደረገው ውይይት የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቤጂንግ ከሚያደርጉት ውይይት ቀደም ብሎ የተደረገ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳ ሚኒስቴር ዋንግ ዩ ከሰርጌ ላቭሮቭ ጋር የነበራቸው ቆይታ በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ለሚደረገው የፊት ለፊት ውይይት የመጨረሻውን ዝግጅት ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ በበኩላቸው፥ በቀጣይ የሚደረገው የሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ስብሰባ የሩስያ እና ቻይና ግንኙነትን ለማጠናከር፣ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስርዓት ግንባታን ለማስፋፋት እንዲሁም የሀገራቱን ዘላቂ ልማት ለማስቀጠል የጋራ ወሳኔዎች የሚተላለፉበት ይሆናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በሩሲያ እና በቻይና መካከል ያለው ከፍተኛ ስትራቴጅካዊ ትብብር እና የቅርብ ቅንጅት ከዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽእኖ የጸዳ እንዲሆን ሁለቱ መሪዎች ወሳኝ ስምምነቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ላቭሮቭ መናገራቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!