Fana: At a Speed of Life!

በሊባኖስ ያለሰነድ ይኖሩ የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ ያለሰነድ ይኖሩ የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ።
 
የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤት ከሊባኖስ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር ነው በተለያየ ምክንያት ያለ ህጋዊ ሰነድ በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገው፡፡
 
ወደ ሀገራቸው የገቡት ዜጎች በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ተመዝግበው ከነበሩ መካከል 80ዎቹ መሆናቸውን ከቆንስላ ጄኔራል ጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.