Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል በ6 ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27 ፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃረሪ ክልል ባለፉት 6 ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን የክልሉን የ6 ወራት የገቢ አፈፃፀምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ፥ በ2014 ዓ.ም በ6 ወራት ውስጥ 593 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለመሰብስብ ታቅዶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ211 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

በዚህም በግማሽ አመቱ 580 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ ከታቀደው እቅድ 97 ነጥብ 8 በመቶ ማሳካት ተችሏልም ነው የተባለው፡፡

300 ሚሊየን ብሩ ከቀጥታ ታክስ፣ 178 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ 35 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች እንዲሁም 65 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ መሆኑንም ተናግረዋል ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ያሳደረው ተፅእኖ እንዲሁም አሸባሪው ህውሓት በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው ጦርነት ምክንያት በንግድ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ ቢያሳድርም በቅንጅት በመሰራቱ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አመላክተዋል፡፡

በቀጣይም እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በማጠናከር በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን 1ነጥብ 64 ቢሊየን ብር ገቢ ለማሳካት ይሰራልም ብለዋል፡፡

በክልሉ 15 ሺህ 548 ግብር ከፋዮች እንደሚገኙ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.