ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቦረና እና ምስራቅ ጉጂ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የእንስሳት መኖ እና የዳቦ ዱቄት ነው።
የተለገሰውን ድጋፍ የጉጂ ዞን አባገዳና ከቦረና ዞን የተወከሉ የሃገር ሽማግሌዎች በመስቀል አደባባይ ተገኝተው ተረክበዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድም ድጋፉን አስረክበዋል።
በቆንጂት ዘውዴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!