Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድሩ በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ እስከ ሚያዚያ ሊቀጥል እንደሚችል ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የተከሰተው ድርቅ እስከ ሚያዚያ ድረስ ሊቀጥል ይችላል ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከሌሎች የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን
ከዩ ኤስኤይድ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሴን ጆንስ ጋር በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉትም ፥ የድርቁ ሁኔታ እስከ ሚያዚያ ድረስ ሊቀጥል ይችላል።

የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ፥ በድርቁ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከምግብ እጥረት አደጋዎች ለመከላከል ስራዎች በመሠራት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ለእንስሳትም መኖ በማቅረብ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የዩኤስኤይድ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሴን ጆንስ በበኩላቸው ፥ ድርጅታቸው በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.