Fana: At a Speed of Life!

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ለተጎዱ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ከ14 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል ውድመት ለደረሰባቸው መቅደላ አምባ፣ ወሎ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የቤተ-ሙከራ ዕቃዎችና ኮምፒውተሮችን አበርክቷል፡፡

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እና የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ዶክተር ዘይቱ ጋሻው ፥ በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፥ ግምታቸው 11 ሚሊየን 984 ሺህ ብር የሚሆን የቤተሙከራ መሳሪያዎች፣ የምግብ ቤት ዕቃዎችና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች ለመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ለእያንዳንዳቸው ግምታቸው 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚሆን የቤተሙከራ መሳሪያዎች ለወሎ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አወል ሰኢድ፥ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.